የልደታ ክ/ከተማ ባህልና ኪነ-ጥበብ ጽ/ቤት በአዋጅ ቁ. 90/2017 መሠረት የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ተሰጥተውታል
- በመንግስት ህንጻና ንብረት አስተዳደር ላይ ለክ/ከተማ አስተዳደሩ የቴክኒክ ድጋፍ ይሰጣል፤ ያማክራል፤
- ስልጣኑ በህግ ለሌላ አካል ወይም ለሌላ የመንግስት መስሪያ ቤት ካልተሰጠ በቀር የክ/ከተማዉን አስተዳደር ህንፃዎችንና ቋሚ ንብረቶችን ይመዘግባል፤ በበላይነት ያስተዳድራል፤ ያድሳል፤ ጥገና የሚያስፈልጋቸውን ህንፃዎች በመለየት እንዲጠገን ያደርጋል፤
- የህንጻና ንብረት አስተዳደር እና አጠቃቀም ዘመናዊ ስርዓትን ይዘረጋል፤ ለታለመለት ዓላማ መዋሉን ያረጋግጣል፤ ምድረ ግቢን ውብና ማራኪ እንዲሆኑ ያደርጋል፤
- የመንግስት ህንፃዎች አጠቃቀም፣ ለተጠቃሚው ያላቸው ተደራሽነት እና ከወጪ አንፃር ውጤታማ መሆናቸውን ያረጋግጣል፤
- የክ/ከተማዉን አስተዳደሩ የመንግስት ተቋማት ለአገልገሎት አሰጣጥ የሚያስፈልጋቸውን ህንፃዎች የኪራይ ደረጃ አጥንቶ ይወስናል፤ ለመንግስት አገልግሎት የሚውሉ ህንፃዎች እንዲገነቡ ያደርጋል፤
- በክ/ከተማዉን ውስጥ ባለቤት የሌላቸው ህንጻና ንብረቶችን አግባብ ባለው ህግ መሰረት ተረክቦ ያስተዳድራል፤
- የመንግስት ህንፃዎች ወጥ የሆነ ስታንዳርድ እና ዲዛይን እንዲኖራቸው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ይሰራል፤ ያስገነባል፤ አፈፃፀሙን ይከታተላል፤
- የህንጻ አስተዳደር ሥራዎች የተቀላጠፉና ውጤታማ እንዲሆኑ የውስጥ አደረጃጀት እና የቢሮ ቁሳቁስ ስታንዳርድ ያዘጋጃል፤ እንዲተገበር ያደርጋል፤
- በመንግስት የንብረት አያያዝ ስርዓት መሰረት የመንግስት ንብረቶች በአግባቡ ስለመያዛቸው እና ጥቅም ላይ ስለመዋላቸው የንብረት ኦዲት ያደርጋል፤
- በጽ/ቤቱ የህንጻና የንብረት ኦዲት ውጤት መሰረት ተገቢው የእርምት እርምጃ ያልወሰዱ የመንግስት መስሪያ ቤቶችን ለይቶ ተጠሪ ለሆነለት ቢሮና ለሚመለከተው አካል ያሳውቃል፤
- አግባብ ባለው ህግ ቋሚ ንብረቶች ዋጋ እንዲወጣላቸው እና በየዓመቱ የዕልቀት ዋጋ እንዲሰላላቸው በማድረግ መንግስት የቋሚ ንብረቶች የያዙትን ዋጋ እንዲያውቅ ያደርጋል፤
- በጽ/ቤቱ በሚያስተዳድራቸው ንብረቶች ላይ የሚፈጸሙ ህገወጥ ድርጊቶችን ይከላከላል፤ ተፈጽሞም ሲገኝ ህጋዊ እርምጃ ይወስዳል ወይም እንዲወሰድ ያደርጋል፤
- የመንግስት ህንፃዎች የሚገነቡበት ቦታ ያስፈቅዳል፤ ይመዘግባል፤ ተገቢውን የይዞታ ማረጋገጫ እና የግንባታ ፈቃድ እንዲሰጥ ያደርጋል፤ ይጠብቃል፤
- የመንግስት ህንፃዎች የሰራተኞች ካፍቴሪያ፣ የጽዳትና ውበት፣ የጥበቃ፣ የመጀመሪያ ህክምና፣ የመንግስት ተሸከርካሪዎች ማቆሚያ፣ የመኪና እጥበት እና የህፃናት ማቆያ አገልግሎቶች ተግባራትን ያከናውናል፡፡