የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2014 ዓ.ም የአገልግሎት ሰጪ ተቋማትን መልሶ ለማደራጀት በወጣ አዋጅ ቁጥር 74/2014 መሰረት የመንግስት ንብረት አስተዳደር ባለሥልጣን እንደገና የተቋቋመ ሲሆን ከተሰጠው ስልጣንና ኃላፊነት መነሻ ለተገልጋዮቹ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በአዲስ መልክ በመለየት አደራጅቷል፡፡ ይህን ኃላፊነትም በብቃት ለመወጣት ዘመናዊ የንብረት አስተዳደር ስርዓት በመዘርጋት፣ ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የከተማዋን እድገት ባገናዘበ በሚመጥን መልኩ የንብረት አስተዳደር ችግሮችን የሚፈታ፣ ወጪ ቆጣቢ የሆነና የመንግስት ሃብት አጠቃቀም ስርአት መዘርጋት የሚያስችል ተደራሽ፣ ቀልጣፋና ውጤታማ በመሆኑ መልኩ አገልግሎቶችን ለመስጠት የሚያስችል አሰራር ዘርግቶ ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል፡
ስለሆነም በልደታ የመንግስት ንብረት አስተዳደር ጽ/ቤት የሚሰጠው አገልግሎት የተገልጋይ ፍላጎትን ማዕከል አድርጎ ይበልጥ ተደራሽ እንዲሆን ለማስቻል የሚሰጡ አገልግሎት አይነቶች፣ አገልግሎቱ የሚሰጥበት ስታንዳርድ፣ አገልግሎቱ የሚሰጥበትን ቦታ እና ከተገልጋይ የሚጠበቁ ቅድመ ሁኔታዎችን በግልጽ በዝርዝር በማስቀመጥ የቢሮው አመራሮችና ሠራተኞች ሊተገብሩትና ሊከተሉት የሚገባ ... ተጨማሪ ያንብቡ
ቅድስት ማቴዎስ , የልደታ ክ/ከተማ የመንግስት ንብረት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ