image
image
image
image
image

የልደታ ክፍለ ከተማ የመንግስት ንብረት አስተዳደር ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸሙን ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ገመገመ።

ጥቅምት 10, 2018
የጽ/ቤቱ ኃላፊ ወ/ሮ ቅድስት ማቴወስ እንደተናገሩት ተቋማትንና ንብረትን በአግባቡ ለማስተዳደር የሚያስችሉ ስራዎችን እየተሰሩ መሆኑንና የተቋማትን ንብረቶች እርጅና ቅናሽ በመስራት ንብረቶች በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲወሉ እየተደረገ ይገኛል። ወ/ሮ ቅድስት አክለውም በ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት በጤና ተቋማት፣በትምህርት ቤቶችና በወረዳዎች እንዲሁም በክፍለ ከተማ ተቋማት ላይ ያሉትን ንብረቶች መረጃ በአግባቡ በማደራጀት ለቁጥጥር አመቺ እንዲሆኑ መሠራቱን ገልጸው በቀጣይም በአፈጻጸማችን ላይ የነበሩትን ጥንካሬዎች በማስቀጠል የተሻለ አፈጻጸም እንዲመዘገብ በመተባበር ልንሰራ የሚገባ መሆኑን ተናግረዋል። የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የህንጻዎችንና ሌሎች ንብረቶች አገልግሎት ላይ መዋል ሲጀምሩ ያላቸውን ዋጋ መግለጽና እርጅና ቅናሽ መስራት የሚገባ መሆኑን ገልጸው ይህ መሆኑ የመንግስትን ንብረት በአግባቡ ለመያዝና ብክነትን ለመቀነስ የሚያስችል አሰራርን ልናጠናክር ይገባል ብለዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች