image
image
image
image
image

የኤሌክትሮኒክስና ፈርኒቸሮችን ጠግኖ በመጠቀም ከትርፍ ወጪና የሀብት ብክነት ለመቀነስ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ተገለፀ።

ጥቅምት 19, 2018
የልደታ ክፍለ ከተማ የመንግስት ንብረት አስተዳደር ጽ/ቤት "መልሶ ጠግኖ የመጠቀም ባህል ለከተማችን ሁለንተናዊ ብልፅግና "በሚል መሪ ሃሳብ ከወረዳ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ሀላፊዎች ፣ከጤና ጣቢያና ከትምህር ቤት ተቋማት ከክፍለ ከተማ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄዷል። የልደታ ክፍለ ከተማ የመንግስት ንብረት ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ቅድስት ማቲዎስ እንደገለፁት መጠገን የሚችሉ የመንግስት ንብረቶችን ጠግኖ መልሶ በመጠቀም ከትርፍ ወጪና የሀብት ብክነትን በጋራ በመስራት መከላከል እንደሚገባ ገልፀዋል። የኤሌክትሮኒክስና ፈርኒቸሮችን ጠግኖ በመጠቀም ትርፍ ወጪና የሀብት ብክነት ለመቀነስ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ የገለፁት ወ/ሮ ቅድስት አያይዘው በቀጣይ በምንሰራቸው ተግባራት ውጤታማ ለመሆን ሁሉም ተጠሪ ተቋማት ሚናቸውን መወጣት ይኖርባቸዋል በማለት ገልፀዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አበራ ተስፋዬ በመድረኩ እንደተናገሩት የመንግስትን ንብረት መልሶ ጠግኖ መጠቀም እንደሚገባ ገልፀው ሃብትን ከብክነት ለመከላከል የሁሉም ዜጋ ሀላፊነት ሊሆን እንደሚገባ ገልፀዋል። የመንግስት ንብረትን ጠግኖ መልሶ ጥቅም እንዲውሉ ማድረግ ተገቢና መንግስት ያለ አግባብ የሚያወጣውን ወጪ በማስቀረት ይገባል ያሉት አቶ አበራ ተስፋዬ አያይዘው በየተቋሙ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራበት ይገባል ሲሉ ገልፀዋል። የመድረኩ ተሳታፊዎችም ተቋማት በቅንጅት በመስራት የተጎዱ የመንግስት ንብረቶችን ጠግኖ መልሶ በመጠቀም የመንግስት ወጭን ማዳን እንደሚገባ አንስተዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች