Welcome to Lideta Subcity Public Property Administration Office!       እንኳን ወደ ልደታ ክ/ከተማ የመንግስት ንብረት አስተዳደር ጽ/ቤት በሰላም መጡ!       ጽ/ቤቱ በልደታ ዘመናዊና ስታንዳርዱን የጠበቀ የንብረት አስተዳደር ስርዓት የዘረጋ ተምሳሌት ተቋም ሆኖ ማየት ይተጋል!

የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2014 ዓ.ም የአገልግሎት ሰጪ ተቋማትን መልሶ ለማደራጀት በወጣ አዋጅ ቁጥር 74/2014 መሰረት የመንግስት ንብረት አስተዳደር ባለሥልጣን እንደገና የተቋቋመ ሲሆን ከተሰጠው ስልጣንና ኃላፊነት መነሻ ለተገልጋዮቹ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በአዲስ መልክ በመለየት አደራጅቷል፡፡ ይህን ኃላፊነትም በብቃት ለመወጣት ዘመናዊ የንብረት አስተዳደር ስርዓት በመዘርጋት፣ ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የከተማዋን እድገት ባገናዘበ በሚመጥን መልኩ የንብረት አስተዳደር ችግሮችን የሚፈታ፣ ወጪ ቆጣቢ የሆነና የመንግስት ሃብት አጠቃቀም ስርአት መዘርጋት የሚያስችል ተደራሽ፣ ቀልጣፋና ውጤታማ በመሆኑ መልኩ አገልግሎቶችን ለመስጠት የሚያስችል አሰራር ዘርግቶ ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል፡

ስለሆነም በልደታ የመንግስት ንብረት አስተዳደር ጽ/ቤት የሚሰጠው አገልግሎት የተገልጋይ ፍላጎትን ማዕከል አድርጎ ይበልጥ ተደራሽ እንዲሆን ለማስቻል የሚሰጡ አገልግሎት አይነቶች፣ አገልግሎቱ የሚሰጥበት ስታንዳርድ፣ አገልግሎቱ የሚሰጥበትን ቦታ እና ከተገልጋይ የሚጠበቁ ቅድመ ሁኔታዎችን በግልጽ በዝርዝር በማስቀመጥ የቢሮው አመራሮችና ሠራተኞች ሊተገብሩትና ሊከተሉት የሚገባ ... ተጨማሪ ያንብቡ

ቅድስት ማቴዎስ , የልደታ ክ/ከተማ የመንግስት ንብረት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ
image description

የጽ/ቤቱ ቡድን መሪዎች

ወ/ሮ አለምፀሀይ በዛብህ ሰ

የስራዎች ሂደት አስተባባሪ

አቶ ጌታቸው ታደሰ

የንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ

አቶ ጓዱ ፈንቴ

የምድረ ጊቢ ቡድን መሪ

ወ/ሮ አልማዝ ኤባ

ፋሲሊቲ ቡድን መሪ

አቶ ዮሴፍ የሺጥላ

ቡድን መሪ

የልደታ ክ/ከተማ መንግስት ንብረት አስተዳደር ጽ/ቤት

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የልደታ ክ/ከተማ መንግስት ንብረት አስተዳደር ጽ/ቤት ከተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት መነሻ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታትና የለውጥ ሥራዎችን ቀጣይነት ለማረጋገጥ የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ በብቃቱና እና በሥነ-ምግባሩ የተመሰገነ የሰው ኃይል እንዲመራ በማድረግ ለተገልጋዮቹ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በአዲስ መልክ በመለየት አደራጅቷል፡፡

በተጨማሪም በጽ/ቤት የሚሰጠው አገልግሎት የተገልጋይ ፍላጎትን ማዕከል አድርጎ ይበልጥ ተደራሽ እንዲሆን ለማስቻል የሚሰጡ የአገልግሎት አይነቶች፣ አገልግሎቱ የሚሰጥበት ስታንዳርድ፣ የሚሰጥበትን ቦታ እና ከተገልጋይ የሚጠበቁ ቅድመ ሁኔታዎችን በግልጽ በዝርዝር በማስቀመጥ የጽ/ቤቱ ሠራተኞች በተቀመጠላቸው ስታንዳርድ መሰረት ፍህታዊና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጡና ተገልጋዮች ምን ዓይነት አገልግሎት በምን ዓይነት ደረጃ ማግኘት እንደሚገባቸው ግንዛቤ በመፍጠር በዚህም ግልፅነትና ተጠያቂነት እንዲኖር፣ በህዝብና መንግስት መካከል መተማመን እንዲፈጠር፣ ልማትና ዲሞክራሲ እንዲያብብ ትልቅ አስተዋጽኦ አላቸው፡፡ በመሆኑም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂት ለመፍታት በምናደርገው ጥረት ባለድርሻ አካላትና ህብረተሱቡ ከጽ/ቤቱ ጎን እንዲቆሙ እናሳስባለን፡፡